History for Home (history as of 28/08/2023 10:44:05 ጥዋት)

መጀመር

  1. የተቀናጀ የይዞታ አስተዳደር መረጃ ስርዓት የድረ-ገጽ ፖርታል ማግኘት

የተቀናጀ የይዞታ አስተዳደር የመረጃስ ርዓት የድረ-ገጽ ፖርታልhttp://www.ADDISLAND.gov.et የሚለውንየድረ-ገጽ አድራሻ በመጠቀም የሚገኝ ሲሆን የሁሉም የስርዓቱ ተጠቃሚዎች ወደ ስርዓቱ መግቢያ ነው፡፡የስርዓቱ ተጠቃሚዎች ከብዛታቸው የተነሳ ሊዘረዘሩ አይችሉም ነገርግን ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

  1. ዜጎች/ደንበኞች፡– ለይዞታ አገልግሎት ለማመልከትና ሂደቱን ለመከታተል፤

  2. ስታፍ፡– ወደ ስርዓቱ ለመግባትና ስራዎችን ለመስራት እንዲሁም የተለያዩ ሪፖርቶችን ለማመንጨት፤

  3. የማኔጅመንት አባላት፡–ወደ ስርዓቱ ለመግባትና የተለያዩ የማኔጅመንት ሪፖርቶችን ለማውጣት፤

  4. ከህዝቡ መካከል ያሉ ሌሎች ተጠቃሚዎች፡-የይዞታ አገልግሎትን መረጃ ማየት እና/ወይም የይዞታ ምስክር ወረቀትን እውነተኝነት መፈተሸ፤

  • ከመሸጥ በፊት ገዥዎች የሚያደርጉት ፍተሻ፤

  • የህግ አስፈጻሚ ወኪሎች የሚያደርጉት ህጋዊ ምርመራ፤

  • ሌሎች፤

የተቀናጀ የይዞታ አስተዳደር የመረጃ ስርዓት የድረ-ገጽ አድራሻ በመጻፍ የሚከተለው ምስል ላይ የሚታየው ኮምፒውተር ላይ ይመጣል፡-

ምስል 3: የተቀናጀ የይዞታ አስተዳደር ስርዓት ትግበራ - የድረ-ገጽ ፖርታል በ XOKA

የድረ-ገጽ ፖርታሉን ለመጠቀም ከይዘቶቹ ጋር መተዋወቅ አለብን፡፡ የሚከተሉት የመነሻ ገጹ ዋና ዋና አካላት ናቸው፡-

  • መመዝገብ – ከማመልከታቸው በፊት ዜጎች/ደንበኞች መመዝገብ ያስፈልጋቸዋል፡፡ስለሆነም ይህ ሊንክ ለመመዝገብ የሚያስፈልገውን ቅጽ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል፡፡ ተጠቃሚውን ተሳታፊ ለመሆንም በኤሌክትሮኒክ ደብዳቤ ማነቃቃት ያስፈልገዋል፡፡

  • መግባት፡– ከምዝገባው ስኬት ቀጥሎ ዜጎች/ደንበኞች/ስታፍ ወደ ስርዓቱ ይገባሉ ይህም ይዞታ ለይዞታ ለማመልከት ወይም የለትከለት ተግባራትን ለማከናወን ነው፡፡

  • የቋንቋ መረጣ()፡– ዜጎች/ደንበኞች/ስታፍ ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲቀይሩ ይረዳቸዋል፡፡

  • መነሻ ገጽ፡– ወደድረ-ገጹፖርታልመግቢያቦታነው፡፡

  • ክፍለ ከተሞች፡– ክፍለከተሞችናበያንዳንዱክፍለከተማየሚሰጡየአገልግሎትዝርዝሮች፤

  • አገልግሎቶች፡-የተመረጠው አገልግሎት የሚገኝበት የይዞታ አገልግሎቶች እና የሁሉም ክፍለ ከተሞች ዝርዝሮች፤

  • አገልግሎቶች በርእስ፡– 25 የይዞታ አገልግሎቶች በ10 ርዕሶች ተደራጅተው፤

  • ዜና፡– የበድረ-ገጽ ይዘት አስተዳዳሪዎች በየወቅቱ የሚታተሙ ዜናዎች፤

  • ዳሽ-ቦርድና ሪፖርቶች፡– የተወሰነ ክፍለ ከተማ፣ የከተማ አስተዳደር፣ ግለሰቦች፣ ቡደኖች፣ ዴስኮች ወዘተ ወደ ተለያዩ ዳሽ-ቦርድና ሪፖርቶች መግቢያ በር፤

  • ጠቃሚ ሊንኮች፡– ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የሚያገናኙ ሊንኮች ናቸው፤

  • መፈለግ፡–በአጠቃላይ የድረ-ገጹ ፖርታል ላይ የሚደረግ ፍለጋ፤

የድረ-ገጽ ፖርታሉን ተጠቅሞ በኦንላይን ከይዞታ ጋር የተያያዙ ግልጋሎቶች ዙሪያ ማመልከት ከፈለጉ ዜጎች/ደንበኞች መጀመሪያ የድረ-ገጽ ፖርታሉ ቀኝ-ጫፍ ላይ የመገኘውን ተመዝገብ (Register) የሚለውን ቁልፍ በመጠቀም መመዝገብ አለባቸው፡፡ ተመዝገብ(Register) የሚለው ምስል ከስር በምስል 4 መመልከት ይቻላል፡፡ 

ተመዝገብ የሚለው ትግበራ ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ደህንነቱ የተጠበቀ የተጠቃሚ ስም፣ ማለፊያ ቃልና ኤሌክትሮኒከ ደብዳቤ አድራሻ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል፡፡ የሰጡትንም መረጃ በመጠቀም ስርዓቱ አጭር የጽሁፍ መልእክት በተጨማሪ ሌሎች የማስታወቂ አገልግሎቶችን የሰጣቸዋል፡፡

  1. የተቀናጀ ይዞታ የድረ-ገጽ ፖርታል ላይ እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል

ምስል 4: የተቀናጀ የይዞታ አስተዳደር ስርዓት - የምዝገባ ስክሪን በ XOKA

ከተመዘገቡ በኋላ ዜጎች/ደንበኞች ወደ ስርዓቱ አዲስ በፈጠሩት መገለጫ መግባት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቀደም ብለው መገለጫው ካላቸው ወደ ስርዓቱ ገብተው አዲስ ትግበራ መጀመር ይችላሉ ወይም በጀመሩት መቀጠል ይችላሉ፡፡ 

ምስል 5: የተቀናጀ የይዞታ አስተዳደር ስርዓት - ወደ ስርዓቱ የመግቢያ በ XOKA

ለዜጎች/ለደንበኞች ኦንላይን የይዞታ ግልጋሎት ትገበራ የሚጀምሩባቸው ሶስት ምርጫዎች አላቸው፡-

  • የክፍለ ከተሞች ዝርዝር

  • የአገልግሎቶች ዝርዝር

  • አገልግሎት በርእስ

የክፍለ ከተሞች ዝርዝር

የክፍለ ከተሞች ዝርዝርን ክሊክ ሲደረግ የሚከተለው ምስል ኮምፒውተር ላይ ይታያል፡

ምስል 6: የተቀናጀ የይዞታ አስተዳደደር ስርዓት ይክፍለ ከተሞች ዝርዝር ማውጫ በ XOKA

ለሆነ ይዞታ አገልግሎት ማመልከት ለሚፈልጉ ዜጎች/ደንበኞችሆነው የይዞታ ግልጋሎቱ የት ክፍለ ከተማ እንደሚገኝ ካወቁ ወደዚህ ገጽ መጥተው ካለው የአገልግሎቶቹ ዝርዝሩ መምጥ ይችላል፡፡

ከክፍለ ከተሞች ዝርዝር በተጨማሪ የአገልግሎቶች ዝርዝር እና የአገልግሎቶች ዝርዝር በርእስ ዝርዝር ዜጎች/ደንበኞች ካሉት ግልጋሎቶች ውስጥ ዜጎች/ደንበኞች መርጠው ማመልከት ይችላሉ፡፡የአገልግሎቶች ዝርዝር የአገልግሎቶችንና የክፍለ ከተሞችን ዝርዝር ይሰጣል ይህም ማመልከት እንዲጀምሩ ያደርጋቸዋል፡፡የአገልግሎቶች ዝርዝር በርእስ ዜጎች/ደንበኞች በቀላሉ የሚልጉት የአገልግሎት ዓይነት እንዲያገኙ በሚል የተከፋፈሉ ግልጋሎቶችን ይሰጣል በተጨማሪም ክፍለ ከተማ እንዲመርጡ ያስችላቸዋል ይህንንም በመጠቀም የማመልከት ሂደቱን መጀመር ይችላሉ፡፡

ምስል 7: የተቀናጀ የይዞታ አስተዳደር ስርዓት የአገልግሎቶች ዝርዝር ማውጫ በ XOKA

የአገልግሎቶች ዝርዝርናየአገልግሎት ዝርዝር በርእስ የጋራ መለያ ባህሪያታቸው ሁለቱም የክፍለ ከተማው የይዞታ አስተዳደር ጽ/ቤቶች ለዜጎች/ደንበኞች የሚሰጡትን የይዞታ አገልግሎቶች ዝርዝር ያሳያሉ፡፡

 

በተጨማሪም ዜጋ/ደንበኛ ማመልከት የሚፈልገውን አገልግሎትና የሚያመክትበትን ክፍለ ከተማ ከመረጠ በኋላ በGoogle Maps, አገልግሎቱን የሚያገኙበትን ክፍለ ከተማ እንዲያዩ ይደረጋሉ፡፡

 

የተጠየቀውን አገልግሎት ማግኘት ማለት ከአዲስ የይዞታ ምስክር ወረቀት አንጻር፣ ከተሻሻለ የይዞታ አገልግሎት አንጻር፣ ከአገልግሎት ማረጋገጫ ደብዳቤ ወዘተ አንፃር የተጠየቀው አገልግሎት የመጨረሻ ውጤት ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ምንም እንኳ ማመልከቻው ኦንላይን ቢሞላም ሁሉም ሂደቶች ዜጋ/ደንበኛ በአካል መምጣት ሳይጠበቅበት ይከናወናሉ፡፡ ክፍያ በአካባቢው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይከፈላል በመጨረሻም ሰነዱን(ደብዳቤ፣ የይዞታ ምስክር ወረቀት ወይም ሁለቱም) ለመውሰድ ዜጋ/ደንበኛ ወደ ክፍለ ከተማ መምጣት ይጠበቅበመታል፡፡ የክፍለ ከተማው የይዞታ አገልግሎት መስጪያ ጽ/ቤት በGoogle Maps አማከኝነት በቀላሉ ዜጋው ማግኘት ይችላል፡፡

  

|<< Back |